March 31, 2020

ኢትዮጵያ ውስጥ ለ33 አመት ያገለገሉት የካቶሊክ ሊቀ-ጳጳስ አንጄሎ ሞሬስቺ ጣልያን ውስጥ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው እንዳለፈ ታውቋል

በኢትዮጵያ የካቶሊክ ሊቀ-ጳጳሶች ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ተሾመ ፍቅሬ ወ/ተንሳኤ ዛሬ እንደነገሩኝ ሊቀ-ጳጳስ አንጄሎ በጋምቤላ ለበርካታ አመታት አገልግለው በ2016 ባጋጠማቸው የልብ እና የኩላሊት ህመም ወደ ጣልያን አምርተው ነበር።

ከትናንት በስቲያ 390 ገደማ ኢትዮጵያውያንን ይዞ ከሳውዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ የጀመረ የሳውዲ አየር መንገድ አውሮፕላን ወደመጣበት እንዲመለስ እንደተደረገ መረጃ ደርሶኛል!

መረጃው እንደሚያመለክተው ይህ የበረራ ቁጥሩ SV-3618 የሆነ እና ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ይዞ ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ ያደረገው አውሮፕላን ወደ ጅዳ ተመልሶ እንዲያርፍ ተደርጓል።

የቀድሞው የቴክሳስ ኮንግረስማን የነበሩት ሮን ፖል ከስድስት ቀን በፊት የኮሮና ቫይረስን "የፈጠራ ወሬ" ብለው አጣጥለውት ነበር

ትናንት ምሽት ደግሞ ልጃቸው የሆነው ሴናተር ራንድ ፖል ቫይረሱ የተገኘበት የመጀመርያው የአሜሪካ ከፍተኛ ፖለቲከኛ ሆኗል። #CoronavirusIsReal

"ከዛሬ ጀምሮ የአ.አ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት የኮሮና ስርጭትን ለመቆጣጠር የተሳፋሪውን ቁጥር 50 በመቶ በመቀነስ አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል።

ህዝባችን በሚሳፈርበት ጊዜ ርቀት ጠብቆ በመቆም የበኩሉን አስተዋፆ እንዲያበረክት አሳስባለሁ"--- የትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ

በኮሮና ቫይረስ ዙርያ አንዳንድ መረጃዎች

ኢትዮጵያ ውስጥ ከገቡ በሗላ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የተረጋገጠው ሁለት ጃፓናውያን ነገ ጠዋት በአውሮፕላን አምቡላንስ ከኢትዮጵያ ወደ ጃፓን እንደሚወሰዱ መረጃ ደርሶኛል።

የኮሮና ቫይረስ የተነሳባት የቻይናዋ ሁቤ ግዛት አዲስ የተጠቂዎች ቁጥር ቀስ እያለ ቀንሶ አሁን ዜሮ እንደሆነ ተሰምቷል

ብሉምበርግ እንደዘገበው አሁን ቻይናን እያሳሰባት ያለው ከሌላ ሀገራት ወደ ሀገሪቱ ሊገባ የሚችል ቫይረስ ነው።

ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ የተጓዙ ሁለት ጣልያናውያን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ተደረጉ

የኬንያው Standard Media ማምሻውን እንደዘገበው የሀገሪቱ ባለስልጣናት ሁለቱን ጣልያናውያን በመጡበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ መልሰዋቸዋል።

"በሀዋሳ ከተማ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የሚነገር አሉባልታ መሰረተ ቢስ ነው" --- የአስተዳደሩ ጤና መምሪያ

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ ቡሪሶ ቡላሾ በከተማዋ ኮሮና ቫይረስ ተጠቂ የሆነ ግለሰብ ስለመኖሩ የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የዩጋንዳው ፕሬዝደንት በህዳሴ ግድብ ዙርያ አስቸኳይ "የአፍሪካ ስብሰባ" እንዲደረግ ጥሪ አደረጉ

ዩዌሪ ሙሴቪኒ ጥሪውን ያደረጉት በቅርቡ ከኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር በተገናኙበት ወቅት እንደሆነ Egypt Independent ዘግቧል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ስለአባይ ከተናገሩት ላይ የተወሰደ:

ግድቡ በግብፅ ላይ ጉዳት እንደማያደርስ የራሳቸው የውሀ ኤክስፐርቶችም፣ ፖለቲከኞቻቸውም ያውቁታል።

የኦሮሚያ ኒውስ ኔትወርክ (ኦኤንኤን) ሁለት ጋዜጠኞቼ በመንግሥት ታሰሩብኝ ብሏል

የታሰሩ ጋዜጠኞችም ደሱ ዱላ እና ዋቆ ኖሌ እንደሚባሉ የቴሌቪዥን ጣቢያው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሶርሳ ደበላ ተናግረዋል።

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ከእስር ተፈተዋል!

የኢትዮጵያ መንግስት ክሳቸው አንዲቋረጥ ካደረገላቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ...

የቻይናው ፕሬዝደንት ዢ ጂንፒንግ ለኢትዮጵያ ምስጋና አቀረቡ

"የኮሮና ቫይረስን ለመዋጋት የቻልነውን ሁሉ እያደረግን ባለንበት በዚህ ወቅት የኢትዮጵያው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሁለት ግዜ መልእክት በመላክ እንዲሁም ስልክ በመደወል የአብሮነት ተምሳሌትነታቸውን አሳይተውናል።

የአዲስ አበባ ከተማ ልዩ መገለጫ ይሆናል የተባለው የመሶብ ታወር ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀመር ተነግሯል!

የመሶብ ታወር ሥራ አስኪያጅ አቶ ፀጋዬ ተክሉ እንደተናገሩት ከዓመት በፊት በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ይፋ የተደረገው የመሶብ ቅርጽ ያለው ታወር ግንባታው ከመጪዎቹ አራት ወራት በኋላ ይጀመራል።

"በዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ ይደርሳል"--- በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

በዘንድሮው ዓመት በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ተቀስቅሶ የነበረውን ረብሻ ተከትሎ በዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ላይ የተለያዩ ዛቻና ማስፈራሪያዎች እየደረሰ መሆኑ ተጠቆመ።

LOAD MORE

Follow Us on

ኮሮናቫይረስ ቤላሩስ፡ በአውሮፓ በኮቪድ-19 የማትሸበር ብቸኛዋ አውሮፓዊት አገር

አሁን አውሮፓ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ማዕከል ነች። ነገር ግን አውሮፓ ውስጥ ሆና ባላስልጣናቷ በአሁኑ ጊዜ ዓለምን እኣስጨነቀ ስላለው የኮሮናቫይረስ ወረርሸኝ ምንም አይነት የተለየ ማስጠንቀቂያም ሆነ ትዕዛዝ...

March 31, 2020

በፓናማ ወንዶችና ሴቶች ተለያይተው ከቤት እንዲወጡ ተደረገ

የማዕከላዊ አሜሪካ አገር ፓናማ ጥብቅ የሆነ የኮሮናቫይረስ የመከላከል እርምጃ መውሰዷን የፈረንሳዩ የዜና ወኪል ዘገበ።

March 31, 2020

የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በዓይን የሚሰራ የሰዓት መቆጣጠሪያ ተግባራዊ አደረገ

የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በዓይን የሚሰራ የሰዓት መቆጣጠሪያ ተግባራዊ አድርጓል፡፡

March 31, 2020

በአዲስ አበባ የታክሲዎችን እንቅስቃሴ የሚቆጣጠር መተግበሪያ ወደ ሥራ ሊገባ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ የሚንቀሳቀሱ የከተማ ታክሲዎችን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የሚረዳ ‹አዲስ ጉዞ› የተሰኘ አዲስ መተግበርያ በሥራ ላይ ለማዋል በሂደት ላይ እንደሆነ ተገለጸ።

March 31, 2020

የአማራ ክልል በ4 ከተሞች ማንኛውም አይነት የህዝብና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እንዳይኖር ተወሰነ

በአማራ ክልል ኮሮና የቫይረስ መከላከል እና መቆጣጠር ኮማንድ ፖስት በአራት ከተሞች ማንኛውም አይነት የህዝብ እና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እንዳይኖር ውሳኔ አሳለፈ።

March 31, 2020

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የጁመዓና ጀመዓ ሶላቶችን ከለከለ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የጁመዓና ጀመዓ ሶላቶችን ከለከለ።

March 31, 2020

ኮሮና፦ የማያውቁት የተፈጥሮ ባላጋራ

የመንግሥትን ዝግጅት ያዩ ዜጎች ከተነገሩት የበለጠ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል ማለት ነው ብለው መጠርጠር ጀምረዋል።

March 30, 2020

የ2020 የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች ተራዘሙ

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በ3 ሃገራት የሚካሄዱ የ2020 የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች መራዘማቸው ይፋ ሆኗል፡፡

March 28, 2020

የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሣ ለአንድ ዓመት ተራዘመ

በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተከትሎ የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ አዘጋጆች ጨዋታው ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ተስማሙ።

March 28, 2020

ኢትዮጵያ ለኢኮኖሚ ማነቃቂያና ለሸቀጦች ግዥ 20 ቢሊዮን ብር መድባለች

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በፍጥነት የመዛመቱና ከግማሽ ሚሊዮን በላይ በዓለም የሚገኙ ሰዎችን በማዳረስ በሺዎች የሚቆጠሩትን ለሞት አብቅቷል፡፡ አሁንም በመዛመት ላይ ይገኛል፡፡

March 30, 2020

ቤንዚን በሕገ- ወጥ መንገድ ሲያጓጉዙ የነበሩ የነዳጅ ማደያ ሥራ አስኪያጆች ቁጥጥር ሥር ዋሉ

በአሶሳ ከተማ ከ10 በርሜል በላይ ቤንዚን በሕገ- ወጥ መንገድ ሲያጓጉዙ የነበሩ ሁለት የተባበሩት እና የኦይል ሊቢያ ነዳጅ ማደያ ሥራ አስኪያጆች በትላንትናው ዕለት ቁጥጥር ሥር ማዋሉን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ።

March 30, 2020

የአምባሳደሮች ምደብ ቦታ ይፋ ተደረገ

የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያን በተለያዩ አገራት የሚወክሉ 15 አዳዲሰ አምባሳደሮችን ሹመት የካቲት 24 ቀን 2012 ዓም ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።

March 26, 2020

በጌዲዮ ከ 1 ሺህ በላይ የብልፅግና ፓርቲ አባላት ለ5 ቀን የሚቆይ ስብሰባ ዛሬ ይጀምራሉ

በጌዲዮ ዞን በሚገኙ 12 ወረዳዎች ስር ከሚገኙ 164 ቀበሌዎች የተወጣጡ 1640 ሰዎች በየወረዳቸው ከዛሬ መጋቢት 14/ 2012 ጀምሮ ለአምስት ቀናት የሚቆይ የብልፅግና ፓርቲ የበታች አመራር ስልጠና ይጀምራሉ።

March 26, 2020

በምእራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች ተቋርጦ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት ዳግም እንዲጀምር መደረጉን የክልሉ መንግስት ገለፀ

በምእራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች ውስጥ በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ተቋርጦ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት ዳግም እንዲጀምር መደረጉን የክልሉ መንግስት ገለፀ።

March 31, 2020

የሶማሊያ ጦር 142 የአልሻባብ ታጣቂዎችን በትላንትናው ዕለት መግደሉን አስታውቋል፡፡

ከሞቱት በተጨማሪ 29 ታጣቂዊች መቁሰላቸውን እንዲሁም 18ቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው የገለፀው፡፡

March 31, 2020

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ

• ዛሬ በበሽታው የተያዙ ታማሚዎች - 3 • በአሁን ጊዜ በለይቶ ማቆያ ያሉ ታማሚዎች - 21 • ፅኑ ህሙማን - 2 • ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ያገገሙ - 2 •...

March 31, 2020

የአገር መከላከያ በሄሊኮፕተር መረጃ የያዙ በራሪ ወረቀቶችን ሊበትን ነው

የአገር መከላከያ ሠራዊት ስለ ኮሮናቫይረስ መረጃ የያዙ በራሪ ወረቀቶችን በሄሊኮፕተር ሊበትን መሆኑን አስታወቀ።

March 31, 2020