August 3, 2020

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአፍሪካ ሕብረት ሰንደቅ ዓላማና መዝሙር ረቂቅ አዋጅን አፀደቀ

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ የተለያዩ አዋጆችን ያፀደቀ ሲሆን የምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአፍሪካ ሕብረት ሰንደቅ ዓላማ፣ መዝሙር እና የአፍሪካ ቀን ረቂቅ አዋጅ አፅድቋል።

የደቡብ ክልል ምክር ቤት የሲዳማ ዞን የአገሪቱ አስረኛ ክልል ሆኖ እንዲደራጅ የሥልጣን ርክክብ ለማድረግ የቀረበውን አጀንዳ ተቀብሎ አጸደቀ።

ምክር ቤቱ አጀንዳውን ያጸደቀው ከደቂቃዎች በፊት በሀዋሳ ከተማ በጀመረው የምክር ቤቱ አምስተኛ ዙር አምስተኛ ዓመት ሁለተኛ አስቸኳይ ጉባኤው ነው ።

በደቡብ ክልል ምክር ቤት የሚገኙ የዎላይታ ሕዝብ ተወካዮች እራሳቸውን ከምክር ቤት አባልነት አግልለዋል

የብሔሩ ተወካይ አባላት ራሳቸውን ከምክር ቤት አባልነት ያገለሉት የዎላይታ ሕዝብ እራሱን በራሱ ለማስተዳደር ያስችለኛል በሚል ላቀረበው በክልል የመደራጀት ጥያቄ ምክር ቤቱ ተገቢውን ምላሽ አልሰጠም በሚል ነው ተብሏል ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአመቱ የተማሪዎች የምረቃ መርሐ ግብር በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ በቪዲዮ እንደሚካሔድ አስታወቀ።

አንጋፋው ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳለው 80ኛው የተማሪዎች የምረቃ መርሐ-ግብር በመጪው ሐምሌ 4 ቀን 2012 ዓ.ም ይካሔዳል።

በጀርመን ከ 4000 ዓመት በላይ ዕድሜ ያለው አፅም ተገኘ

በጀርመን ብራንደንቡርግ በቁፋሮ የተገኘው ይህ አጽም ከ 4 ሺህ አመታት በፊት ባልተለመደ ሁኔታ የተቀበረ የአንዲት ሴት አፅም መሆኑን ተመራማሪዎች ገልፀዋል።

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን አጠናቀቀ

በትናንትናዉ ዕለት የ12 የምክር ቤት አባላቱን ያለመከሰስ መብት ያነሳው የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን መደበኛ ጉባኤ በዛሬው ዕለት አጠናቋል።

የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ማጭበርበር እና ዘረፋ ወንጀል አከሸፈ

ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ረጅም ጊዜ በመውሰድ በተለያየ መንገድ ክትትል ሲያደርግበት የነበረው እና በጉዳዩም ላይ በቂ መረጃ ሲያሰባስብበት የቆየው ዓለም አቀፍ የገንዘብ ዝውውር ሥርዓትን በመጠቀም 110 ሚልዮን ዶላር የማጭበርበር እና የዘረፋ የወንጀል ሙከራ በቁጥጥር ስር እንዲውል አድርጓል።

በትግራይ ክልል በኮሮና የተያዙ ተጨማሪ ሁለት ሰዎች መገኘታቸውን የትግራይ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ይፋ ባደረገው መግለጫ በክልሉ ዛሬ በተደረጉ 86 የላብራቶሪ ምርመራዎች ሁለት በኮሮና የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን አስታውቋል።

ድሬዳዋ ቅጣትና ግጭት

የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ድንጋጌን ያላከበሩ አካላት በገንዘብ መቀጣታቸውን አስታወቀ።

ሩሲያ በአንድ ቀን 9,623 ሰዎች በኮሮና መያዛቸው በምርመራ ማረጋገጧን አስወቀች።

የአገሪቱ ግንባታ ምኒስትር ቭላድሚር ያኩሼቭ በኮሮና ተይዘው ሆስፒታል ሲገቡ ምክትላቸው በተሕዋሲው መያዛቸው ታውቋል።

ደቡብ አፍሪቃዊዉ የፀረ-አፓርታይድ ታጋይ አረፉ

ታዋቂዉ ደቡብ አፍሪቃዊ የፀረ-አፓርታይድ ታጋይ ዴኒስ ጎልድንበርግ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር እስክንድር ነጋ የእጅ ስልክ ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በፖሊስ ቊጥጥር እንደሚገኝ ዐስታወቀ።

አቶ እስክንድር ኮሮናን ለመከላከል የወጣውን አካላዊ መራራቅ (ማኅበራዊ መራራቅ) ደንብ ሳይጥሱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ስልካቸውን እንደወሰደባቸው አምነስቲ ጽፏል።

ሰርግ ላይ የፈነዳ ቦንብ ሰው ገደለ!

በአማራ ክልል ጥንቃቄ በጎደለው ኹኔታ ሰርግ ላይ በተተኮሰ ጥይት እና በፈነዳ ቦንብ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

ኮሮና በፈረንሣይ ሐኪም ቤቶችን 1 ቢሊዮን ዶላር ግድም አስወጣ

የፈረንሳይ ሕዝባዊ ቤተ-ኅሙማን በኮሮና ተሐዋሲ የተጠቊ ሰዎችን ለማከም ሀገሪቱ እስከ 980 ሚሊዮን ዩሮ ገንዘብ ማውጣታቸው ተገለጠ።

የትግራይ ክልል መንግስት ምርጫው መካሄድ አለበት አለ

የትግራይ ክልል ኮምኒኬሽን ቢሮ ሐላፊ ወይዘሮ ሊያ ካሳ ከዚህ ቀደምም ኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ላይ ሆና ጭምር ምርጫ የማካሄድ ልምድ ነበራት ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል በትግራይ የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፌደራሉ መንግስት ሀገራዊ ምርጫ የማያካሂድ ከሆነ የትግራይ ክልል መንግስት ለምርጫ ዝግጅት ማድረግ አለበት ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ የምታቀርባቸው ሸቀጦች በባቡር እና በመርከብ የሚጓጓዙበትን ዋጋ በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ በከፍተኛ ደረጃ ቀነሰች።

ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት የአምራቾችን ሸቀጦች እስከ ጅቡቲ ወደብ የኢትዮ-ጅቡቲ አክሲዮን ማኅበር በነፃ እንዲያጓጉዝ መንግሥት ወስኗል።

የኢራን እና የዩናይትድ ስቴትስ ፍጥጫ

በኮሮና ተሐዋሲ ሥርጭት የተነሳ ለጊዜው ጋብ ብሎ የነበረው የኢራን እና የዩናይትድ ስቴትስ ፍጥጫ መልኩን በመቀየር ላይ ይመስላል።

LOAD MORE

Follow Us on

የድሮ ዘፈን ላይ የቀረበ አጭር ትንታኔ

( በእውቀቱ ስዩም’)

August 1, 2020

እንዴት አደራችሁ !

ዛሬ በመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው 1 ሺ 441ኛው ዒድ አል አድሐ አረፋ በዓል ነው ።

August 1, 2020

ፌስቡክ ‘መጥፎ’ መልእክት የያዙ ጽሑፎች ላይ ምልክት ማድረግ ሊጀምር ነው

በፌስቡክ ላይ የሚደረገው የተቃውሞ ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠሉን ተከትሎ ድርጅቱ ‘መጥፎ’ መልእክት የያዙ ጽሑፎች ላይ ምልክት ማድረግ እንደሚጀምር አስታውቋል።

June 27, 2020

ሊደደርሱ የነበረውን የሳይበር ጥቃቶችን ማክሸፍ ተችሏል-- ኢመደኤ

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ፣ ስነ ልቦናዊ እና ፖለቲካዊ ጫና ለመፍጠር የተቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ማክሸፉን የኢትዮጵያ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አስታወቀ

June 27, 2020

200 ሕጻናት አንድ ላይ በመሆን ችግኝ ተክለዋል

'በልጆች ልብ ውስጥ የዛፍ ችግኝ እንትከል' እንትከል በሚል መሪ ሃሳብ 200 ሕጻናት ዛሬ በኢሲኤ ፓርክ ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጠዋል።

August 1, 2020

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለ1 ሺህ 441ኛው የዒድ አል-አድሀ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ

ለመላው ሙስሊም ወገኖቼና ለተቀረው ኢትዮጵያዊ ሁሉ፣ እንኳን ለ1441 ኛው ዓመተ ሒጅራ፣ ለታላቁ የዒድ አል-አድሐ / የዐረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን ለማለት እወዳለሁ። ዒድ ሙባረክ

August 1, 2020

የሕገ መንግሥቱን ክፍተት በሕገ መንግሥት ትርጉም የመመለስ ጅማሮ የገጠመው ተቃርኖ

ሕገ መንግሥቱ ባስቀመጠው የአምስት ዓመት የጊዜ ማዕቀፍ ውስጥ ምርጫ ማከናወን የማይቻልበት ከአቅም በላይ ሁኔታ ቢከሰትና በሥልጣን ላይ ያሉት የመንግሥት አካላት ሕጋዊ የሥራ ዘመን ቢጠናቀቅ፣ አገር የማስተዳደር ኃላፊነት የማን ሊሆን እንደሚችል ሕገ መንግሥቱ ያስቀመጠው ምንም ዓይነት ድንጋጌ አለመኖሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ ልሂቃንንና መላውን የፖለቲካ ማኅበረሰብ ትኩረት ስቦ በስፋት እያነጋገረ ይገኛል።

May 11, 2020

የኮቪድ 19 ፖለቲካ ሽንቁር ውስጥ ያስገባቸው የዓለም ጤና ድርጅትና ዋና ዳይሬክተር

በቻይና ሁቤ ግዛት ለመጀመርያ ጊዜ የተገኘው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ (ኮቪድ 19) የበርካታ ዜጎችን ሕይወት የነጠቀ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ያጠቃ፣ የዓለምን ኢኮኖሚ ያናጋና መንግሥታትን የፈተነ የወቅቱ ክስተት ነው፡፡

May 11, 2020

አርሰናል የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን ለ14ኛ ጊዜ አሸነፈ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ትናንት ምሽት በተካሄደው የኤፍ ኤ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ቼልሲን ሁለት ለአንድ በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሄኗል፡፡

August 2, 2020

የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ ።

August 2, 2020

የፈረንሳይ ጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት እድገት በፈረንጆቹ 2020 ሁለተኛ ሩብ አመት በ13 ነጥብ 8 በመቶ ቀንሷል

የፈረንሳይ ጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት እድገት በፈረንጆቹ 2020 ሁለተኛ ሩብ አመት በ13 ነጥብ 8 በመቶ መቀነሱን የሃገሪቱ ብሄራዊ ስታቲስቲክስ ቢሮ አስታውቋል፡፡

July 31, 2020

ወደ ውጭ ከተላኩ ሥጋ እና የወተት ተዋጽኦዎች 72 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኘ

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ወደ ውጭ ከተላኩ ሥጋ እና የወተት ተዋጽኦዎች 72 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ የሥጋ እና የወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

July 31, 2020

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል መንግስትን አስጠነቀቀ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል መንግስት ምርጫ ለማካሄድ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ “በአፋጣኝ እንዲያቆም” አሳሰበ።

July 30, 2020

በትግራይ ክልል ምርጫ እንሳተፋለን ያሉ...

በትግራይ ክልላዊ ምርጫ ላይ እንደሚሳተፉ እስካሁን ድረስ ካሳወቁ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የክልሉ ገዢ ፓርቲ ህወሓት ፣ ሳልሳይ ወያኔ ትግራይ ፣ ባይቶና ትግራይና ውድብ ናፅነት ትግራይ ይገኙበታል።

July 30, 2020

አምስት የአልሸባብ ታጣቂዎች ተገደሉ

የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር በአገሪቱ ደቡባዊ ግዛት በታችኛው የጁባ አካባቢ አምስት የአልሸባብ ታጣቂዎች መግደሉን አስታውቋል፡፡

August 3, 2020

በሕንድ የተመረዘ አልኮል የጠጡ 86 ገደማ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ

በሰሜናዊ ሕንድ ፑንጃብ ግዛት የተመረዘ አልኮል የጠጡ 86 ገደማ ሰዎች መሞታቸውን የግዛቲቱ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

August 3, 2020

ተጨማሪ 707 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ የ28 ሰዎች ሕይወትም አልፏል

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 7 ሺህ 607 የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 707 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸውና የ 28 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትረት ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

August 2, 2020

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 469 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 7,358 የላብራቶሪ ምርመራ 469 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል።

August 2, 2020