March 31, 2020

የ70 ዓመቱ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔትናሁ የኮሮና ቫይረስ የላብራቶሪ ውጤታቸው ነጻ(ኔጋቲቭ) መሆናቸውን አሳይቷል።

ውጤቱ ነጻ መሆናቸውን ቢያሳይም ከጤና ሚንስትር ተጨማሪ ማረጋገጫ እና ፈቃድ እስኪነገራቸው ራሳቸውን ለይተው ያቆያሉ።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በለይቶ መቆያ መወሰናቸው ተሰማ፡፡

ኔታንያሁ በለይቶ መቆያ የተወሰኑት የቅርብ አማካሪያቸው በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው በምርመራ ከተረጋገጠ በኋላ እንደሆነ ታይምስ ኦፍ ኢዝራኤል ፅፏል፡፡

በጀርመን የአንዲት ግዛት የገንዘብ ሚኒስትር የነበሩት ቶማስ ሸፈር ራሳቸውን አጠፉ።

የገንዘብ ሚኒስትሩ ራሳቸውን ያጠፉት የኮሮና ቫይረስ ባመጣው ጣጣ ነው ተብሏል።

ኢኳቶሪያል ጊኒ ውስጥ የ10 ዓመት ታዳጊ በቫይረሱ መያዟ ተነግሯል።

ይህች ታዳጊ የጉዞ ታሪኳ እንደሚያሳየው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ማርች 13 ነበር ከስፔን ወደ ኢኳቶሪያል ጊኒ የተመለስችው።

የጎዳና ተዳዳሪዎችን ከኮሮና ቫይረስ ስጋት ለመጠበቅ ከጎዳና ላይ ማንሳቱን እንደማያስበው የአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ተናገረ፡፡

ይልቁንም ለጎዳና ተዳዳሪዎች ውሃ እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ በማቅረብ ራሳቸውን እንዲጠብቁ እያደረግኩ ነው ብሏል፡፡

የኢምግሬሽን፣ ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ከነገ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ፓስፖርት መስጠት አቆማለሁ አለ፡፡

ኤጀንሲው አዲስም ሆነ የሚታደስ ፓስፖርት ከነገ ጀምሮ እንደማይሰጥ የነገሩን የሕዝብ ግንኙነት እና ኮምኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ደሳለኝ ተሬቻ ናቸው፡፡

የኮሮና ቫይረስ ለመግታት ትምህርት ሚንስትር እና ተጠሪ ተቋማቱ ሰራተኞችቤታቸው ሆነው ስራቸውን እንዲሰሩ ወሰነ

የኮሮና ቫይረስ ለመግታት ትምህርት ሚንስትር እና ተጠሪ ተቋማቱ ከ1544 ሰራተኞች 196(12.7%) ብቻ በማስቀረት ቀሪዎቹ ሰራተኞች ቤታቸው ሆነው ስራቸውን እንዲሰሩና መንግስት ስርጭቱን ለመከላከል በሚያደርገው ጥረት የበኩላቸውን...

የጀርመኗ መራሄተ መንግሥት አንጌላ መርክል በምርመራ ከኮሮና ቫይረስ ነጻ መሆናቸው መረጋገጡን የጀርመን መንግሥት ቃል አቀባይ ተናገረ

አርብ ዕለት ለመርክል የፀረ-ኒሞኒያ አምጪ ተህዋስ ክትባት የሰጣቸው ዶክተር በኮሮና መያዙን ተከትሎ፣ መራሄተ መንግስቷ ራሳቸውን አግልለው ነበር፡፡ የ65 ዓመቷ መርክል በቀጣይ ቀናትም በተደጋጋሚ ይመረመራሉ ተብሏል፡፡

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ዳሽን ባንክ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉን ተናገረ፡፡

ባንኩ የኮሮናን ስጋት ለመቀነስ በዋና ስራ አስፈፃሚው የሚመራ ግብረ ሃይል ማቋቋሙንም ተናግሯል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ታይተውበት ለምርመራ ወደ ለይቶ ማቆያ ገብቶ የነበረው ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር የሚሠራ የውጭ ዜጋ ከቫይረሱ ነፃ መሆኑ ተረጋገጠ።

ቦርዱን በሎጂስቲክስ ሥራ እንዲያግዝ በተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት (UNDP) የተቀጠረው ይኸው ግለሰብ፣ 2 ጊዜ ጥልቅ ምርመራ ተደርጎለት፣ ከኮሮና ቫይረስ ነፃ ሆኖ መገኘቱን ሸገር ከቦርዱ ሰምቷል።

ከቻይና የመጡ 4 ኢትዮጵያዊያን የኮሮና ቫይረስ ይኖርባቸዋል በሚል ተጠርጥረው ወደ ለይቶ ማከሚያ ማዕከል መግባታቸው ተነገረ፡፡

ከአራቱ ኢትዮጵያዊያን መካከል 2 ወረርሽኙ ከተቀሰቀሰበት ውሃን ከተማ የመጡ መሆናቸው ታውቋል፡፡

የጨዋታዎች ጥቆማ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ቀን 9:00 ይደረጋሉ።

የኢትዮጵያ ፕረምየር ሊግ የጨዋታ መርሃ ግብሮች

6ኛ ሳምንት ላይ የደረሰው ፕሪምየር ሊጉ ትናንት በሰበታ ከተማ እና ወላይታ ድቻ መካከል በተደረገ ጨዋታ ተጀምሯል።

ተወዳዳሪ ሀገር በቀል የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ለኢትዮጵያ ብልፅግና

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ሙያተኞች፣ ዘርፉ በሙስና እንዲተበተብና ተወዳዳሪነቱ እንዲቀጭጭ ራሳችሁ ፈቅዳችሁ በምታደርጉት ሙስና ሳቢያ ዘርፉ እየተጎዳ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሙያዎች ወቀሳ አዘል ምክር ሰጥተዋል፡፡

የስፖርት ወሬዎች

ታህሳስ 22፣2012

የኢትዮጵያና የሩሲያን የወታደራዊ ቴክኒክ ዘርፎች የሚያበረታ ጉባኤ በሩሲያ ተካሄደ፡፡

የኢትዮ-ሩሲያ የወታደራዊ የቴክኒክ ትብብር የጋራ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ በሞስኮ መደረጉን የተናገረው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው፡፡

LOAD MORE

Follow Us on

ኮሮናቫይረስ ቤላሩስ፡ በአውሮፓ በኮቪድ-19 የማትሸበር ብቸኛዋ አውሮፓዊት አገር

አሁን አውሮፓ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ማዕከል ነች። ነገር ግን አውሮፓ ውስጥ ሆና ባላስልጣናቷ በአሁኑ ጊዜ ዓለምን እኣስጨነቀ ስላለው የኮሮናቫይረስ ወረርሸኝ ምንም አይነት የተለየ ማስጠንቀቂያም ሆነ ትዕዛዝ...

March 31, 2020

በፓናማ ወንዶችና ሴቶች ተለያይተው ከቤት እንዲወጡ ተደረገ

የማዕከላዊ አሜሪካ አገር ፓናማ ጥብቅ የሆነ የኮሮናቫይረስ የመከላከል እርምጃ መውሰዷን የፈረንሳዩ የዜና ወኪል ዘገበ።

March 31, 2020

በአዲስ አበባ የታክሲዎችን እንቅስቃሴ የሚቆጣጠር መተግበሪያ ወደ ሥራ ሊገባ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ የሚንቀሳቀሱ የከተማ ታክሲዎችን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የሚረዳ ‹አዲስ ጉዞ› የተሰኘ አዲስ መተግበርያ በሥራ ላይ ለማዋል በሂደት ላይ እንደሆነ ተገለጸ።

March 31, 2020

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ የዲጂታል ማስተግበሪያ ወደ ስራ ገባ

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ የዲጂታል ማስተግበሪያ ወደ ስራ ማስገባቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

March 31, 2020

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የጁመዓና ጀመዓ ሶላቶችን ከለከለ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የጁመዓና ጀመዓ ሶላቶችን ከለከለ።

March 31, 2020

ከአየር መንገድ ጠፍተው ወደ ኅብረተሰቡ ተቀላቅዋል የተባሉ ግለሰቦች የገቡት የግዴታ ለይቶ ማቆየት ከመተግበሩ በፊት ነው - የጤና ሚኒስቴር

መጋቢት 15 ቀን 2012 ዓ.ም ከዱባይ ወደ አዲስ አበባ የመጡ አንድ መንገደኛ ወደ ሀገር ከገቡ በኋላ ከአየር መንገድ በመጥፋት ወደ ኅብረተሰቡ ተቀላቅለዋል በሚል በማኅበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው መረጃ ላይ የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማጣራት ማካሔዱን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

March 31, 2020

ኮሮና፦ የማያውቁት የተፈጥሮ ባላጋራ

የመንግሥትን ዝግጅት ያዩ ዜጎች ከተነገሩት የበለጠ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል ማለት ነው ብለው መጠርጠር ጀምረዋል።

March 30, 2020

የ2020 የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች ተራዘሙ

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በ3 ሃገራት የሚካሄዱ የ2020 የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች መራዘማቸው ይፋ ሆኗል፡፡

March 28, 2020

የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሣ ለአንድ ዓመት ተራዘመ

በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተከትሎ የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ አዘጋጆች ጨዋታው ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ተስማሙ።

March 28, 2020

ኢትዮጵያ ለኢኮኖሚ ማነቃቂያና ለሸቀጦች ግዥ 20 ቢሊዮን ብር መድባለች

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በፍጥነት የመዛመቱና ከግማሽ ሚሊዮን በላይ በዓለም የሚገኙ ሰዎችን በማዳረስ በሺዎች የሚቆጠሩትን ለሞት አብቅቷል፡፡ አሁንም በመዛመት ላይ ይገኛል፡፡

March 30, 2020

ቤንዚን በሕገ- ወጥ መንገድ ሲያጓጉዙ የነበሩ የነዳጅ ማደያ ሥራ አስኪያጆች ቁጥጥር ሥር ዋሉ

በአሶሳ ከተማ ከ10 በርሜል በላይ ቤንዚን በሕገ- ወጥ መንገድ ሲያጓጉዙ የነበሩ ሁለት የተባበሩት እና የኦይል ሊቢያ ነዳጅ ማደያ ሥራ አስኪያጆች በትላንትናው ዕለት ቁጥጥር ሥር ማዋሉን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ።

March 30, 2020

የአምባሳደሮች ምደብ ቦታ ይፋ ተደረገ

የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያን በተለያዩ አገራት የሚወክሉ 15 አዳዲሰ አምባሳደሮችን ሹመት የካቲት 24 ቀን 2012 ዓም ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።

March 26, 2020

በጌዲዮ ከ 1 ሺህ በላይ የብልፅግና ፓርቲ አባላት ለ5 ቀን የሚቆይ ስብሰባ ዛሬ ይጀምራሉ

በጌዲዮ ዞን በሚገኙ 12 ወረዳዎች ስር ከሚገኙ 164 ቀበሌዎች የተወጣጡ 1640 ሰዎች በየወረዳቸው ከዛሬ መጋቢት 14/ 2012 ጀምሮ ለአምስት ቀናት የሚቆይ የብልፅግና ፓርቲ የበታች አመራር ስልጠና ይጀምራሉ።

March 26, 2020

በምእራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች ተቋርጦ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት ዳግም እንዲጀምር መደረጉን የክልሉ መንግስት ገለፀ

በምእራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች ውስጥ በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ተቋርጦ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት ዳግም እንዲጀምር መደረጉን የክልሉ መንግስት ገለፀ።

March 31, 2020

የሶማሊያ ጦር 142 የአልሻባብ ታጣቂዎችን በትላንትናው ዕለት መግደሉን አስታውቋል፡፡

ከሞቱት በተጨማሪ 29 ታጣቂዊች መቁሰላቸውን እንዲሁም 18ቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው የገለፀው፡፡

March 31, 2020

ወደ አፋር ክልል የሚገባ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ እንደማይኖር የክልሉ መንግሥት አስታወቀ

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከዛሬ ጀምሮ ወደ አፋር ክልል የሚገባ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ እንደማይኖር የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።

March 31, 2020

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 25 መድረሱን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለፈው 24 ሰአታት ውስጥ በ66 ሰዎች ላይ ባደረገው የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች መኖራቸው መረጋገጡን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

March 31, 2020