June 4, 2023

በኢትዮጵያ 700 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 655 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል

September 15, 7:04 pm | @EBC


ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 10 ሺህ 24 የላቦራቶሪ ምርመራ 700 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 65 ሺህ 486 ደርሷል። በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 655 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 25 ሺህ 988 ሆኗል። ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ13 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 35 ደርሷል። በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 38 ሺህ 461 ሰዎች መካከል 280 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል። በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 157 ሺህ 292 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።