June 4, 2023

በኢትዮጵያ የመጀመርያው የኮረና ቫይረስ መመርመርያ ኪት ማምረቻ ፋብሪካ ዛሬ ተከፍቷል!

September 13, 11:16 am | @EBC


ፋብሪካው በኢትዮጵያና በቻይናው ቪጂአይ ሀልዝ ትብብር የተቋቋመ ሲሆን በዓመት 10 ሚሊየን ኪቶችን ያመርታል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የፋብሪካው መገንባት በአፍሪካ ሶስተኛ ላይ የደረሰውን የመመርመር አቅም በማሳደግ የተሻለ የመከላከል ስራ ለመስራት ያግዛል ብለዋል። ኢትዮጵያ ፍላጎቷን ካሞላች ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በመላክ እንደአህጉር በሽታውን የመከላከልን ተግባር ታግዛለች ብለዋል። በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፖርክ የተገነባው ፋብሪካው ኮረና ከጠፋ በኃላ የወባና ቲቢ የመመርመርያ ኪቶችን እንደሚያመርት ተገልጿል። በኢትዮጵያና በቻይናው ቪጂአይ ሀልዝ የተገነባው ፋብሪካ ውጤታማ እንዲሆን ከፍተኛ ስራ ለሰሩት ዶክተር አርከበ እቁባይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና አቅርበዋል።