June 4, 2023

ኢዜማ ሊሰጠው የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ለሁለተኛ ጊዜ ተከለከለ፡፡

August 31, 3:10 pm | @Sheger FM


የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ እንዳሉት ጋዜጣዊ መግለጫው የተከለከለው መግለጫ የሚሰጥበት ቦታ የሆነው ራስ ሆቴል ከሰላም ሚኒስቴር የተፃፈ ደብዳቤ ስጡኝ በማለቱ ፤ የሰላም ሚኒስትር ደግሞ ደብዳቤ ለመፃፍ ባለመፍቀዱ ነው ሲሉ ነግረውናል፡፡ ፓርቲው ለሁለተኛ ጊዜ መግለጫ እንዳይሰጥ ስለተከለከለ፣መግለጫውን በፅ/ቤቱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ እንደሚሰጥ አቶ ናትናኤል ፈለቀ ነግረውናል፡፡ ሸገር ይህንኑ ጉዳይ ለማጣራት ወደ ሰላም ሚኒስትር ቢሮ ደውዬ ተነገረኝ እንዳለው፣ የሚኒስትሯ ፅህፈት ቤት ፈቃዱን የሚሰጠው አካል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚኒስትሮች ኮሚቴ መሆኑን ጠቅሶ፣ ለኢዜማ ደብዳቤው ያልተፃፈለት ፣ሚኒስትሯ ስለሌሉ ነው ብሏል፡፡ ጽሕፈት ቤቱ አክሎም በደብዳቤው ላይ የሚፈርሙት ሚኒስትሯ ስለሌሉ ነው እንጂ፣ኢዜማ ፈቃድ አልተከለከለም ብለዋል፡፡ [Sheger FM]