June 4, 2023

ቢያንስ በ53 ሺህ ይህ ተህዋስ የተገጠመላቸው የቴክኖ ስልኮች ኢትዮጵያ፣ ካሜሩን፣ ግብፅ፣ ጋና እና ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መሸጣቸው ተነግሯል።

August 26, 9:57 am | @BBC Amharic


የኮምፒውተር ተህዋስ [ማልዌር] የተገጠመላቸው በሺዎች የሚቆጠሩ የቻይና ስሪት የሆኑ ስልኮች አፍሪካ ውስጥ መቸብቸባቸው ተሰምቷል። አፕስትሪም የተሰኘ አንድ ተቋም ነው ይህን ይፋ ያደረገው። ቢያንስ በ53 ሺህ ይህ ተህዋስ የተገጠመላቸው የቴክኖ ስልኮች ኢትዮጵያ፣ ካሜሩን፣ ግብፅ፣ ጋና እና ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መሸጣቸው ተነግሯል። የስልኮቹ አምራች የሆነው ትራንዚሽን የተሰኘ ኩባንያ ተህዋሱ የተገጠመው ከእኔ እውቅና ውጪ በአከፋፋዮች ነው ይላል። አፕስትሪም የተሰኘው የመሰል ተህዋሶች አጋላጭ ድርጅት በዚህ አይስማማም። "ይህ ማልዌር [የኮምፒውተር ተህዋስ] ሚሊዮኖችና ገቢያቸው አናሳ የሆኑ ሰዎች በሚገዙት ስልክ ላይ መሰል ተህዋስ ያለ ተጠቃሚዎች መገጠሙ ኢንዱስትሪው ምን ያክል የሰዎችን ግላዊነት እየተጋፋ እንዳለ የሚያሳይ ነው" ይላሉ የአፕስትሪም ባለሙያ የሆኑት ጄፍሪ ክሊቭስ። 'ትሪያዳ' የተሰኘው ተህዋስ አንድሮይድ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ የሚገጠም ሲሆን 'ኤክስሄልፐር' የተባለ ኮድ ተጠቅሞ ከተጠቃሚዎች እውቅና ውጪ ያሻውን የሚያደርግ ነው። የሰዎችን ማንነት የሚለየው ቴክኖሎጂ እያከራከረ ነው ሞና ሊሳ "ነፍስ ዘራች" ሰዎችን በፊት ገጽታቸው "ጉግል" ማድረግ ሊጀመር ነው ይህ ማልዌር ብዙ ጊዜ ተጠቃሚዎች ሳያውቁ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን የሚቀላቀል ነው። ይህ ተህዋስ ሞባይል ስልክዎ ላይ ያለዎትን ገንዘብ [የአየር ሰዓት] ያለ ፈቃድዎ የሚወስድ ነው። በርካታ የአፍሪካ አገራት ውስጥ የበይነ መረብ ክፍያ የሚፈፀመው በአየር ሰዓት ነው። አፕስትሪም የተሰኘው ተቋም ቢያንስ 200 ሺህ ስልኮች ያለፈቃዳቸው 'ሰብስክራይብ' ካደረጓቸው አገልግሎቶች እንዲወጡ አድርጓል። ትራንዚሽን ሆልዲንግስ የተሰኘው ተንቀሳቃሽ ስልክ አምራች ኩባንያ ቻይና ውስጥ ካሉ ግዙፍ ኩባንያዎች አንዱ ሲሆን አፍሪካ የምርቶቹ ቁጥር አንድ ገዢ ናት። ቴክኖ፤ ችግሩ ያረጀና ያፈጀ ነው። ከሁለት ዓመት በፊት ቀርፌዋለሁ ይላል። ለቢቢሲ ጉዳዩን የተመለከተ የጽሑፍ መግለጫ የላከው ድርጅቱ፤ "ቴክኖ ደብለዩ2 ስልኮች ያላቸው ሰዎች መሰል ችግር እንዳያጋጥማቸው መጫን የሚችሉት መተግበሪያ [አፕሊኬሽን] አለ። ወደ ቴክኖ ሱቆች መጥተው እርዳታ መጠየቅም ይችላሉ" ይላል። ከወራት በፊት አንድ ሌላ ድርጅት ተመሳሳይ ችግር ያለባቸው ዩኤምኤክስ የተሰኙ የቻይና ምርት የሆኑ ስልኮች ላይ ማግኘቱ አይዘነጋም። ይህ ስልክ አሜሪካ ውስጥ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሰዎች በመንግሥት መከፋፈሉ ይታወሳሉ። በፈረንጆቹ 2016 ራያን ጆንሰን የተሰኙ ተመራማሪ 700 ሚሊዮን አንድሮይድ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ማልዌር እንደተገጠመባቸው ይፋ አድርጎ ነበር። ማልዌር ማለት ስልኮችና ሌሎች የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ ከተጠቃሚዎች እውቅና ውጪ የሚገጠመው ተህዋስ ሲሆን መረጃ ከመመዝበር አልፎ ስልኮችንና ኮምፒውተሮች ከጥቅም ውጪ ሊያደርግ ይችላል። #BBC