June 4, 2023

ቲክቶክ የትራምፕ እገዳ ላይ ህጋዊ እርምጃ ሊወስድ ነው

August 23, 10:31 am | @FANA


ቲክቶክ የዶናልድ ትራምፕ እገዳ ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ፡፡ የቻይናው ተንቀሳቃሽ ምስል አጋሪ ቲክቶክ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኩባንያው በአሜሪካ እንዳይሰራ የጣሉትን እገዳ ለመቃወም ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ማስታወቁ ተነግሯል፡፡ የትራምፕ እገዳ ከቲክቶክ ባለቤት ባይስ ዳንስ ጋር የሚደረግ ግብይትን ከመስከረም ወር አጋማሽ ጀምሮ ይከለክላል፡፡ በዋሽንግተን የሚገኙ ባለስልጣናትም ኩባንያው በአሜሪካ ተጠቃሚዎች በኩል መረጃዎችን ለቻይና መንግስት ሊያስተላልፍ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው ፡፡ በዚህም የኩባንያው ቃል አቀባይ የህግ የበላይነት ወደ ጎን አይባልም ለዚህም የፕሬዝዳንቱን ትዕዛዝ ለመቃወም ወደ ፍርድ ቤት እናመራለን ብለዋል፡፡ የቲክቶክ ህጋዊ እርምጃም በዚህ ሳምንት እንደሚጀምር ይጠብቃል ነው የተባለው፡፡ አጭር ተንቀሳቃሽ ምስል ማጋሪያ ቲክቶክ በአሜሪካ 80 ሚሊየን ተጠቃሚዎች አሉት ፡፡ ምንጭ፡-ቢቢሲ