March 20, 2023
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 19 ሺህ 776 የላቦራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 368 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በአጠቃላይ በአገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 39 ሺህ 33 ደርሷል። በሌላ መልኩ በትናንትናው ዕለት 567 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በአገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 14 ሺህ 480 ሆኗል። ካለፉት 24 ሰዓታት ምርመራ የ25 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በኮሮናቫይረስ የተነሣ የሟቾች ቁጥር 662 ደርሷል። በአሁኑ ወቅት 251 ሰዎች በጽኑ ሕክምና ላይ ሲገኙ፣ 23 ሺህ 889 ደግሞ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች መሆናቸው ተገልጿል። በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካዛሬ ድረስ 736 ሺህ 904 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።