March 20, 2023
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው ሺህ 19 ሺህ 769 የላቦራቶሪ ምርመራ 982 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በአጠቃላይ በአገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 29 ሺህ 876 ደርሷል። በሌላ መልኩ በትናንትናው ዕለት 322 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በአገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 12 ሺህ 359 ሆኗል። ካለፉት 24 ሰዓታት ምርመራ የ19 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በኮሮናቫይረስ የተነሣ የሟቾች ቁጥር 528 ደርሷል። በአሁኑ ወቅት 217 ሰዎች በጽኑ ሕክምና ላይ ሲገኙ፣ 16 ሺህ 687 ደግሞ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች መሆናቸው ተገልጿል። በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካዛሬ ድረስ 609 ሺህ 463 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።