September 28, 2020

ወደ ውጭ ከተላኩ ሥጋ እና የወተት ተዋጽኦዎች 72 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኘ

July 31, 10:39 am | @FANA


የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኃይለስላሴ ወረስ ለኢዜአ እንደገለጹት አብዛኛው ገቢ ከበሬ፣ ፍየል እና የበግ ሥጋ ምርት ውጤቶች የተገኘ ነው፡፡ ቀሪው ገቢ ደግሞ ከሌሎች እንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦ መሆኑን ጠቁመው በዚህም ወተት፣ ማር፣ ሰም እና ዓሳ ወደ ውጭ መላካቸውን ተናግረዋል፡፡ እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ በሚያዚያ እና በግንቦት ወራት ከኢትዮጵያ ወደ ዱባይ እና ሳዑዲ ዓረቢያ የተላከ የዘርፉ ወጪ ንግድ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ ከኢትዮጵያ ወደ ሃገራቱ የሚደረገው በረራ ከመቋረጡ በፊት በቀን የ100 ቶን የሥጋ ፍላጎት እንደነበር ያወሱት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ሃገራቱ ሥጋና የሥጋ ውጤቶችን ከኢትዮጵያ ለማስገባት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ በኮሮናቫይረስ እና በእንስሳት እጥረት ሳቢያ የበረራ አገልግሎት መቋረጡ ከዘርፉ ለማግኘት የታቀደውን 124 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማሳካት እንቅፋት መሆኑንም አስረድተዋል፡፡