September 25, 2020

ተጨማሪ 760 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል

July 24, 8:54 pm | @huleAddis


ዶክተር ሊያ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባለፉት 24 ሰአታት የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉንም አስታውቀዋል፡፡ ይህን ተከትሎም በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 200 ደርሷል ነው ያሉት፡፡ ከዚህ ባለፈም ባለፉት 24 ሰአታት 140 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን ይህን ተከትሎም 5 ሺህ 785 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡ በተጨማሪም 68 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ለ364 ሺህ 322 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 12 ሺህ 693 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡