September 25, 2020

በኢትዮጵያ 24 ሰዓታት 409 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ9 ሰዎች ሕይወት አልፏል

July 23, 6:36 pm | @huleAddis


በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 11 ሺህ 933 መድረሱንም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በትዊተር ገፃቸው ባወጡት መረጃ አመላክተዋል። ከዚህ ባለፈ የ9 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 197 መድረሱንም አመላክተዋል። በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 139 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 5 ሺህ 645 መድረሱም ተገልጿል።