September 28, 2020

የ10 ዓመት ህጻን ልጁን የደፈረው አባት በ9 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቱን የካማሽ ከተማ አስ/ር ፖሊስ አስታወቀ!


ግለሰቡ ነዋሪነቱ ካማሽ ከተማ 02 ቀበሌ ዕለቱ ሰኞ ታህሳስ 08/04/2012 ዓ/ም በግምት ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ የህጻኗ እናት ቤተሰብ ሞቶባት ለሃዘን በሄደችበት ወቅት ከመጠን በላይ ጠጥቶ ሰክሮ በመምጣት የ10 ዓመቷን ህጻን ልጁን ከደበደባት በኋላ አስገድዶ የደፈራት መሆኑን ነው ዋ/ኢ/ር ቃበታ መልካ የገለጹት። ፖሊስም ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውሎ የሰውና የህክምና ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ለካማሽ ወረዳ ዐ/ህግ ያስተላለፈ ሲሆን ዐቃቢ ህጉም ከፖሊስ የደረሰውን የምርመራ መዝገብ ከተመለከተ በኃላ በወ/ል/መ/ቁ/ 122/12 ክስ በመመስረት ለካማሽ ወረዳ ፍ/ቤት አስተላልፏል፡፡ የካማሽ ወረዳ ፍ/ቤትም የቀረበለትን ክስ ሲመረምር ከቆየ በኃላ ግለሰቡ የመከላከል መብቱ ተጠብቆለት መከላከል ባለመቻሉ የዐቃቢ ህግን ማስረጃ በመንተራስ ፍ/ቤቱ በ17/10/2012 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሹ ጥፋተኛ መሆኑ በመረጋገጡ በ9/ዘጠኝ/ ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የካማሽ ከተማ አቤቱታ መቀበል መመርመር ዋና ስራ ሂደት ኃላፊ ዋ/ኢ/ር ቃበታ መልካ ገልፀዋል። ምንጭ፦ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ኮሚኒኬሽን