September 28, 2020

'ኤዲ5-ኤንኮቭ' የኮቪድ-19 ክትባት

June 29, 3:59 pm | @BBC Amharic


'ኤዲ5-ኤንኮቭ' (Ad5-nCoV) የተባለው ክትባት ፣ አካልን ከሽታውን በማስተዋወቅና እንዲከላከል በማድረግ ፣ የመከላከል አቅምን በመገንባት ሰዎች በቫይረሱ እንዳይያዙ ያደርጋል ወይም አያደርግም የሚለውን ለመፈተሽ እየተሞከሩ ካሉ 150 ክትባቶች መካከል አንዱ ነው። ክትባቱ በመከላከያ ኃይሉ የሕክምና ሳይንስ አካዳሚ ስር በሲኖ ባዮሎጂክስ የባዮቴክኖሎጂ ተቋም የተሰራ ሲሆን በጎ ፈቃደኛ በሆኑ ሰዎች ላይ እንዲሞከር በሚል ለክልኒክ ሙከራ የገባ የመጀመሪያው ክትባት ነው። በጥናቱ 108 አዋቂዎች በበጎ ፈቃደኝነት የተሳተፉ ሲሆን ክትባቱ ጉዳት የማያደርስ እንዲሁም የመከላከል አቅምን እንደሚያዳብር መረጋገጡ በሕክምና ጆርናሉ ላንሴት ላይ ተዘግቧል። ነገር ግን ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች ኮሮናቫይርስን እንዳይያዙ የሚያደርግ የመከላከል አቅም ያዳብራሉ ወይ የሚለው ላይ ማረጋገጫ አልተገኘም። ለወታደሮቹ ክትባቱን መስጠት ተመራማሪዎችን እንደሚረዳም ተነግሯል። እስካሁን ድረስ ለሰፊው ሕዝብ የሚያገለግል ክትባት ገና አልተሰራም -