July 8, 2020

ጃፓን በኢትዮጵያ ኮቪድ-19 ለመከላከል የሚውል 4 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገች

June 29, 2:33 pm | @huleAddis


በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካይ አዴል ኮደር “ከጃፓን ያገኘነው እገዛ በአስፈላጊ ጊዜ የደረሰ ነው፤ መንግስት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በህፃናትና ችግር ባጠቃቸው ቤተሰቦች ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የሚያደርገውን ጥረት ያግዛል” ብለዋል። የጃፓን መንግስት ያደረገው ድጋፍ ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ 750 ሺህ ለሚሆኑ ህፃናትና ሴቶች የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ የጤና እና ንፅህና አጠባበቅ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የሚከናወነውን ጥረት ያግዘዋል ተብሏል። ENA