July 8, 2020

የኩፍኝ በሽታ የክትባት ዘመቻ ሊካሄድ ነው

June 29, 12:59 pm | @FANA


ቢሮው ዘመቻውን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ እድሜያቸው ከ9 ወር እስከ 5 አመት ለሆናቸው ህፃናት ከሰኔ 23 ቀን እስከ ሐምሌ 2 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ክትባቱ ይሰጣል ብሏል፡፡ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ ክትባቱ በተጠቀሱት ቀናት በሁሉም ጤና ተቋማት እና ጊዜያዊ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡ በክትባቱ ወቅት ህፃናት ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎችም ልጆቻቸውን በማስከተብ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ማሳሰባቸውን ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡