July 8, 2020

የጀርመን ቡንደስሊጋ ፍፃሜውን ዛሬ ያገኛል


በመጨረሻው ቀን የሚጠበቁ ኩነቶች ውስጥ ላለመውረድ እና በደረጃ ሰንጠረዡ አራት ውስጥ ለመጨረስ የሚደረገው ትንቅንቅ በጉጉት ይጠበቃል :: ቦርስያ ሞንችንግላድባህ ፣ ሌቨርኩሰን ፣ ዎልፍስበርግ ፣ ሆፈኒየም በአውሮፓ የውድድር መድረክ ላይ የሚያሳትፋቸውን ውጤት ለማስመዝገብ ሲፋለሙ ፎርቹና ዱሰልዶርፍ እና ቨርደር ብሬመን በሊጉ ለመቆየት የሚያደርጉት ጨዋታዎች ይጠበቃሉ ::