September 25, 2020

ኢትዮጵያ ከሳተላይት የምታመጣውን መረጃ ለመሸጥ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ

June 12, 4:27 pm | @huleAddis


የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰለሞን በላይ፣ ከዚህ ቀደም በቻይናውያን ሲከወን የቆየው የሳተላይት ቁጥጥር ሥራ በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ባለ ሞያዎች እየተካሔደ ነው ብለዋል። ሳተላይቷ መረጃ መላክ ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ደረጃውን የጠበቀ መረጃ ያለማቋረጥ እየተሰበሰበ መሆኑንም ወና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ሳተላይቷን በማምጠቅ መረጃ ለማግኘት የምታወጣውን ወጪ ከማስቀረት ባለፈ መረጃ በመሸጥ ገቢ ማግኘት መጀመሯን የገለጹት ዶ/ር ሰለሞን፣ ሳተላይቷ የምታመጣውን መረጃ ለሚፈልጉ አካላት ለመሸጥ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ጠቁመዋል። የምስል ግዥ ፍላጎት ላቀረቡ አገሮች ምላሽ መስጠት እንደተጀመረ ገልጸው፣ አሠራሩን ቀላል ለማድረግ ጥረት መደረጉንም አመልክተዋል። #ENA