September 28, 2020

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መሰብሰብ የነበረብኝን 1.5 ቢሊየን ብር በኮቪድ-19 በሽታ ምክንያት መሰብሰብ አልቻልኩም አለ።

June 11, 1:39 pm | @Sheger FM


ይህም የሆነበት ምክንያት ተበዳሪዎችን ለማበርታት እንደሆነ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዛሬ ለጋዜጠኞችን ተናግሯል። የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የወለድ ምጣኔ ማስተካከያ ማድረጉንም ሰምተናል። አነስተኛ እና መካከለኛ ማይክሮፋይናንስ ተቋማት፣ በቱር ኦፕሬተር እና ለየት ባሉ ዘርፎች ለተሰማሩ ትልቁን የወለድ ቅነሳ አግኝተዋል ተብሏል። የወለድ ምጣኔውም ከ 11.5 ወደ 7.5 ዝቅ መደረጉንም ባንኩ ተናግሯል። ይህንንም ማድረጉ የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ከ460 ሚሊየን ብር በላይ የወለድ ገቢ አሳጥቶታል ተብሏል። የልማት ባንክ የገንዘብ እጥረት ለገጠማቸው የማይክሮፉይናንስ ተቋማት ወደ ሁለት ቢሊየን ብር መመደቡ ይታወቃል።