September 25, 2020

የአማዞን  ኩባንያ ፖሊስ የፊት ገጽታ መለያ ቴክኖሎጂውን እንዳይጠቀም ከለከለ

June 11, 1:35 pm | @FANA


ኩባንያው ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው የሲቪል መብት ተሟጋቾች በስለላ ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ የዘር አድልዎ ሊፈጠሩ ይችላሉ የሚሉ ስጋቶችን በማስቀመጣቸው ነው ተብሏል። ከዚያም ባለፈ አፍሪካ አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በነጭ ፖሊስ መሞቱን ተከትሎ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ላይ ጫናዎች እየበረቱ  መምጣታቸውን ተከትሎ መሆኑ ተነግሯል ። ሆኖም የቴክኖሎጂ ኩባንያው ከሰዎች ሕገወጥ ዝውውር ጋር የተያያዙት ድርጅቶች ቴክኖሎጂውን መጠቀም ይችላሉ ብሏል። የቴክኖሎጂ ኩባንያው በሰጠው መግለጫ÷ “መንግስት የፊት ገጽታ መለያ  ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ሥነ-ምግባርን  የሚመለከቱ  ጠንካራ ደንቦችን ማዘጋጀት አለበት  ሲል ገልጿል ። ኩባንያው አያይዞም ለአንድ ዓመት የህግ አስከባሪ አካላት የፊት ገጽታ መለያ ሶፍትዌሩን  እንዳይጠቀሙ መደረጉ የአሜሪካ ህግ አውጪዎች ቴክኖሎጂውን እንዴት እንደሚጠቀሙ የሚቆጣጠር ህግ ለማውጣት እድል እንዲያገኙ  ያደርጋል ብሏል። በተያያዘም በዚህ ሳምንት አይ.ቢ.ኤምኤም የተባለው  የቴክኖሎጂ ኩባንያም “ለጅምላ ክትትል ወይም ለዘር ልዩነት” የፊት መለያ  ሶፍትዌር ማቅረቡን እንደሚያቆም ተናግሯል ። የኢቢኤም ዋና ሥራ አስፈፃሚ አርቪንድ ክሪሽና ለኮንግረስ በፃፉት ደብዳቤ ÷ “ዘረኝነትን መዋጋት ከምንግዜም በላይ አስቸኳይ ነው” እናም ኩባንያው ከፖሊስ ማሻሻያ ፣ ኃላፊነት ያለው የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ አቅምን ማጎልበት እና የትምህርት ዕድሎች ላይ ከኮንግረሱ ጋር ለመስራት ይፈልጋል ብለዋል። በነዚህ የፊት ገጽታን ለይቶ ማሳያ  ቴክኖሎጂ  ላይ የተደረጉ ጥናቶች  እንደሚያመለክቱት አብዛኛዎቹ ስልተ ቀመሮች ከነጭ ሰዎች ፊት ይልቅ የጥቁሮችን ፊት በትክክል የመለየት ዕድላቸው ከፍተኛ  ነው በሚል ሲተች ቆይቷል። ከጆርጅ ፍሎይድ ሞት በኋላ ፖሊሶች የሚጠቀሙት ስልቶች እና ህግ አስከባሪ አካላት የቴክኖሎጅ አጠቃቀም ላይ  ከፍተኛ ትኩረት እየተደረገ መሆኑም ተመላክቷል። ምንጭ፡- ቢ.ቢ.ሲ