September 25, 2020

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኦንላይን ቴክኖሎጂ አሰራር ስርዓትን መጠቀም በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

June 2, 5:11 pm | @FANA


ውይይቱን ያካሄዱት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር አብርሐም በላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ዛሬ በጎበኙበት ወቅት ነው። በውይይታቸውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና አየር መንገዱ የኦንላይን ቴክኖሎጂ የአሰራር ስርዓትን ለመከተልና አብሮ መስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ከአየር መንገዱ ስራ አስኪያጅ አቶ ተወልደ ገብረ ማሪያም ጋር መክረዋል። አቶ ተወልደ ገብረማሪያም ተቋማቸው አብዛኛዎቹን የአየር መንገዱ የቲኬት መሸጫ ቢሮዎችን በመዝጋት ወደ ኦንላይን ቴክኖሎጂ እየተሸጋገሩ መሆናቸውን ጠቅሰው÷ በሌሎችም የአየር መንገዱ የፋይናንስና የሰው ኃይል ጨምሮ እንዲሁም ሌሎች አሰራሮቻቸውን በኦንላይን በማድረግ የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ ለመሆን እየተሰራ ነው ብለዋል። አቶ ተወልደ አያይዘውም አየር መንገዱ የግብይት አሰራር ስርዓታቸውን ወደ ኦንላይ የቴክኖሎጂ ስርዓት መቀየር ለሚፈልጉ ተቋማትም ልዩ ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ገልጸዋል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብርሐም÷ አየር መንገዱ አብሮ ለመስራትና ሌሎች ተቋማትን ለመደገፍ ላሳየው ቀና ፍላጎት ማመስገናቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።