July 8, 2020

በግለሰቦች ተወስዶ የቆየውን 46 ሺህ ሄክታር መሬት ከ60 በላይ ለሚሆኑ አባዎራ አርሶ አደሮች ተመለሰ

May 25, 6:41 pm | @Walta


በስነ ስርአቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከዚህ በኋላ ባዶውን የሚያድር መሬት አይኖርም፤ ሁሉም ይታረሳል ያሉ ሲሆን፣ አሁን መሬታቸው የተመለሰላቸው አርሶ አደሮችም መሬቱን በማልማት ራሳቸውን ከመጥቀም ባለፈ ምርት አቅራቢ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል ፡፡ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ የሚደረገውን የመሬት ወረራ ሁሉም ህብረተሰብ ከመንግስት ጋር በጋራ በመሆን ህገ ወጦችን መካለከል አለበት ያሉ ሲሆን አርሶ አደሮችም ይህን ቦታ ለማልማት እንጂ ለመጋጨት ምክንያት እንዳታደርጉት ሲሉ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡