September 28, 2020

በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ አብነት ተብሎ የሚጠራው ሰፈር የተወሰነ ቦታ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ አካባቢው በጥብቅ ቁጥጥር ውስጥ ገባ፡፡

May 25, 10:26 am | @Sheger FM


የጤና ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም በሰጠው መግለጫ አብነት አካባቢ የሚገኝበት የልደታ ክፍለ ከተማ፣ በአዲስ አበባ ከፍተኛ የኮሮና ታማሚ ያለበት መሆኑን መናገሩ ይታወሳል፡፡ ዛሬ የአካባቢው ነዋሪዎች በመኖሪያ ቤታቸው ተወስነው እንዲቆዩ ስለተደረገበት ሁኔታ ዝርዝር መረጃ ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮም ሆነ ከጤና ሚኒስቴር ለማግኘት ለጊዜው ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፡፡