August 3, 2020

በኢትዮጵያ 30 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

May 22, 2:12 pm | @huleAddis


ቫይረሱ የተገኘባቸው 26 ወንድ እና 4 ሴት ናቸው። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከ15 እስከ 60 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው። ቫይረሱ የተገኘባቸው 18 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 3 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 4 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 3 ሰዎች ከትግራይ ክልል እንዲሁም 2 የደንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ናቸው። የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦ • የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 9 • በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 17 • የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው - 4 ተጨማሪ መረጃ ፦ በትላትናው ዕለት 5 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገመ ሲሆን አጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሃያ ስምንት (128) ደርሷል።