September 28, 2020

በጀርመን ከ 4000 ዓመት በላይ ዕድሜ ያለው አፅም ተገኘ

May 22, 12:55 pm | @DW


ግኝቱን ያደረጉት አርኪኦሎጂስቶቹ ፊሊፕ ሮዝኮሽንኪና እና ክሪስቶፍ ሪዚጎታ እንደገለፁት አፅሙ የተገኘው መቃብር ስፍራ ሳይሆን በመኖሪያ አቅራቢያ በሚገኝ አንድ ጉድጓድ ውስጥ ተጠቅሎ ነው፡፡አፅሙ መቃብር ቦታ ያልተገኘው ሴትዮዋ ሆን ብላ በዚህ መንገድ በመቀመጧ ሳይሆን እንዳልቀረ ተመራማሪዎቹ አመልክተዋል። በዚህ የተነሳ ምርምሩ ያልተለመደና አስደሳች ነው ብለውታል። ተመራማሪዎቹ እንዴት እንደሞተች እና ለምን ባልተለመደ ሁኔታ እንደተቀበረ ለማወቅ ተጨማሪ ምርምር እንደሚያደርጉ የጀርመኑ ዜና ወኪል ዘግቧል። አፅሙ የተገኘው ለንፋስ ሀይል ሥራ ቁፋሮ በሚደረግበት ወቅት ከበርሊን ከተማ 102 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው ኡከርማርክ አውራጃ ነው ፡፡ አፅሙ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ 2 200 እስከ 2 500 ባለው ጊዜ ውስጥ የተቀበረ ነው ተብሎ እንደሚታመን የብራንደንበርግ ግዛት የታሪክ ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ለጀርመን የዜና አውታር ገልጿል። ሴትየዋ የተቀበረችበት ያልተለመደ መንገድም ግኝቱን ከፍተኛ ሳይንሳዊ ጠቀሜታ እንዲኖረው ያደርገዋል ብለዋል ፡፡