September 28, 2020

የጤና ሚኒስትሯ የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

May 22, 12:49 pm | @FANA


በመልዕክታቸው ሕዝበ ሙስሊሙ በረመዳን የጾም ወቅት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ያሳየውን ጥንቃቄ በበዓሉ ወቅትም መድገም እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል። የበዓሉን ግብይት ርቀትን በመጠበቅ፣ የፊት ጭምብል በማድረግና የእጅ ንጽህናን በመጠበቅ ኅብረተሰቡ እንዲያከናውንም አሳስበዋል። በበዓሉ ዕለትም ከቤተሰብ ጋር ማክበር፣ የበሰሉ ምግቦችን መጠቀም እንዲሁም እርድን በተመለከተም ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።