September 28, 2020

ተቋርጦ የነበረው የጀርመን ቡንደስሊጋ ትናንት ሲጀመር ዶርቱሞንድ ተቀናቃኙ ሻልክን 4ለ0 አሸንፏል


ትናት ከተከናወኑት ጨዋታዎች መካከል ሲጠበቅ የነበረው የከተማ ተቀናቃኞቹ ቦሩሲያ ዶርቱሞንድ እና ሻልክ 04 ያደረጉት ጨዋታ ሲሆን ባለሜዳው ዶርቱሞንድ 4ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡ ለዶርቱሞንድ ጎሎቹን ኤርቪን ሃላንድ፤ጎሬሮ ሁለት እና ቶርጋን ሀዛርድ አስቆጥረዋል፡፡ ዶርትሙንድ ጨዋታውን ማሸነፉን ተከትሎ ከመሪው ባየር ሙኒክ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ አጥቧል። በሌሎች ጨዋታዎች ዎልፍስበርግ ኦግስበርን 2 ለ 1፣ኸርታ በርሊን ሆፈኒየምን 3 ለ 0 ሲያሸንፍ፣ዱሰልዶልፍ ከፓደርቦን 0 ለ 0 ፣አርቢ ሌፕዚግ ከፍራይበርግ 1 ለ1 ፣ኢንትራ ፍራንክፈርት በቦሩሲያ ሞንቼግድባህ 3 ለ 1 ተረቷል። ዛሬ የሊጉ መሪ ባየር ሙኒክ ከ ዩኒየን በርሊን፤ኮሎኝ ከሜንዝ የሚጫወቱ ይሆናል፡፡ የጀርመን ቡንደስሊጋ ከተላላቆቹ የአውሮፓ ክለቦች መካከል ቀድሞ ወደ ሊግ ጨዋታ መመለሱን አረጋግጧል፡፡ የቫይረሱ ስርጭት በመጠኑ መቀነሱን ተከትሎ ሌሎች ሊጎችም ከሰኔ ወር በኋላ ቀሪ የሊግ ጨዋታዎቻቸውን ለመጨረስ አቅደዋል፡፡ ቢቢሲ ስፖርት /ኢዜአ