September 28, 2020

ግብፅ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ጋር በተገናኘ ስሞታዋን እና ለፀጥታው ምክር ቤት የሰደደችውን ደብዳቤ የኢትዮጵያ መንግስት እንደተመለከተው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሸገር ነግሯል፡፡

May 6, 12:36 pm | @Sheger FM


ኢትዮጵያ ይህን ጉዳይ በሶስቱ አገሮች በጋራ ውይይት እንደሚፈታ ታምናለች ብለዋል፡፡ እስከ ዛሬ በነበረው ውይይት ላይ አስፈላጊውን ሁሉ ስታደርግ ነበር ያሉን ወሬውንም የነገሩን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቃል አቀባይ ፅ/ቤት ተጠባባቂ ዋና ቃል አቀባይ አቶ አምሳሉ ትዕዛዙ ናቸው፡፡ ግብፅ ጉዳዩን ወደ ተባበሩት መንግስታት ብትወስደውም የኢትዮጵያ መንግስት ይህ አካሄድ ይጠቅማል ብሎ እንደማያስብ ተጠባባቂ ዋና ቃል አቀባዩ ለሸገር ነግረዋል፡፡