September 25, 2020

ኩባንያው የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ መስራቱን አስታወቀ

May 4, 12:20 pm | @Walta


የኩባኒያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ሳሙዔል ይትባረክ ለዋልታ እንደገለጹት መሳሪያው ከውጭ ሃገር የሚገባውን የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ ሙሉ በሙሉ ከመተካቱም ባሻገር በተሻለ ደረጃ መጠቀም የሚያስችል ነው፡፡ መሳሪያው በይዘቱ አነስ ተደርጎ የተሰራ ሲሆን በዋጋ ደረጃም ከውጭ ከሚመጣው መሳሪያ በ90 ከመቶ ቅናሽ እንዳለውም ስራ አስፈጻሚው ጠቁመዋል፡፡ የዘርፉ ሐኪሞችና መካኒካል መሃንዲሶች ለ20 ቀናት ባደረጉት ጥረት መሳሪያውን ለመስራት እንደተቻለ አቶ ሳሙዔል ተናግረዋል፡፡ ስራው እንዲሳካ ከጤና ሚኒስቴር እና ከሚመለከታቸው አካላት ማበረታቻ እንደተደረገላቸውም ተገልጿል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የፈጠራ ስራዎች እንዲሰሩ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡