September 28, 2020

የኢትዮጵያ ብሄራዊ አልኮል እና አረቄ ፋብሪካ የተያዘው ሳምንት ሳያልቅ የንፅሕና መጠበቂያ አልኮል እና ሳኒታይዘር ማምረት እጀምራለሁ አለ፡፡

April 2, 5:36 pm | @Sheger FM


የብሔራዊ አልኮል እና አረቄ ፋብሪካ በየዕለቱ ከሚያመርተው አልኮል በተጨማሪ በቀን ሩብ ሊትር መጠን ያለው 24 ሺ የፕላስቲክ ጠርሙስ ሳኒታይዘር በጥቂት ቀናት ጊዜ ውስጥ አምርቶ ለገበያ እንደሚያቀርብ ተናግሯል፡፡ በ3 ቀን ውስጥም ያመረትኩትን የንፅህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር በገበያው ታገኙታላችሁ ያሉን የብሔራዊ አልኮል እና አረቄ ፋብሪካ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን አባተ ናቸው፡፡ ይኸው የሚመረተው ሳኒታይዘርም ከንፁህ አልኮል እንደሚዘጋጅ ሀላፊው ነግረውናል፡፡ የአልኮል ፋብሪካው፣ አቅም በፈቀደ መጠን ዕለት ተዕለት ከምናመርተው አልኮል 3 እጥፍ፣ በየቀኑ 5 ሺ ሊትርም እያቀረብን ነው ብሏል፡፡ ይህም ምርት በ3 እጥፍ ቢጨምርም በቂ እንዳልሆነ አቶ መስፍን ለሸገር ነግረዋል፡፡ የፋብሪካው ስራ አስፈፃሚ ንጹህ አልኮልንም ለፅዳት አገልግሎት መሸጥ ጀምሬያለሁ ብሏል፡፡ (ተህቦ ንጉሤ)