September 28, 2020

የነቀምቴ ከተማ የቀድሞ የደህንነት ቢሮ ኃላፊ ተገደሉ

March 25, 8:35 pm | @BBC Amharic


አቶ ተሾመ ገነቲ መኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ በጥይት ተመተው መገደላቸውን ጉዳዩን ከሚያውቁ ሰዎች ማወቅ ተችሏል። ነገር ግን የነቀምቴ ከተማ የአስተዳድር እና ደህንነት ቢሮ ኃላፊን ማን እንደገደላቸው እስካሁን አልታወቀም። የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ደህንነት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ግን አቶ ተሾመ "በጥይት መመታታቸው ሰምቻለሁ ከዚህ በተጨማሪ ሌላ መረጃ የለኝም" ብለዋል። በጉዳዩ ላይ ከከተማው እና ከክልሉ ባለስልጣናት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ተጨማሪ መረጃዎችን እንደደረሱን የምናቀርብ ይሆናል።