March 31, 2020

ዩኒሴፍ ለ30ሺህ አባወራዎች የንፅህና መጠበቂያ ለገሰ

March 24, 5:53 pm | @Walta


የዩኒሴፍ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወ/ሮ ወሰኔ ሙላቱ እንዳሉት ዜጎች እራሳቸውን እና ማህበረሰቡን ከቫይረሱ መጠበቅ አለባቸው እንዲሁም ቫይረሱን ለመከላከል አንዱ መንገድ የሆነው የእጅ ንጽህና በሳሙና እና በውሃ ሁል ጊዜ በመታጠብ መጠበቅ ሲሆን በዚህ ረገድ ልገሳው በአዲስ አበባ በቫይረሱ መስፋፋት ለሚከሰት አደጋ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ይረዳል፡፡ በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስን (ኮቪድ19) ስርጭትን ለመዋጋት መንግስት እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ወኪል የገለፁ ሲሆን ኢትዮጵያ የኮርና ቫይረስ በሽታ እንዳይስፋፋ ለማድረግ ዝግጁነቷን አጠናክራለች የዚህ ልገሳ ወጤትም ይህንኑ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡ ልገሳው የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎችን ለመግዛት አቅም ለሌላቸው ሰዎች ቫይረሱን በመዋጋት ረገድ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡