March 20, 2023
March 17, 2:02 pm | @Tikvah Ethiopia
ድራጎን የተባለው ከባድ ዝናብ ባለፈው ሳምንት ጥሎ 20 ሰዎችን የገደለ ሲሆን በመጨረሻ አሌክሳደርያ አካባቢ ሀይቅ ሰርቶ ተቀምጧል፡፡ ይኸው ከፍተኛ የውሃ መጠን 5 ሚሊዮን ስኬር ሜትር በሚሆን መሬት ላይ የተኛ ሲሆን በሀገሪቱ ባለፈው 40 አመት ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነው ተብሏል። ታዲያ አንዳንድ የግብጽ ፖለቲከኞች ይህንን የተኛውን የጎርፍ ውሃ ቆጥቦ በመያዝ ለእርሻ አገልግሎት መጠቀም እንደሚቻል እየተናገሩ ነው፡፡ እንደውም የግብጽ ፓርላማ አባል የሆኑት አብዱል ሀዲ አል ቃስቢ የአየር ንብረት ለውጡ ግብጽ ሌሎች የውሀ አማራጮችን እንድታይ ማስገደድ አይቀርም ብለዋል፡፡