March 20, 2023
March 14, 1:11 pm | @Tikvah Ethiopia
- ሳውዲ አረቢያ ዓለም አቀፍ በረራዎች ለቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት እንዲታገዱ ትዕዛዝ አስተላልፋለች። በሳውዲ በአሁን ሰዓት በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ 86 ሰዎች ይገኛሉ። - የቫይረሱ ስርጭት እየተገታባት ነው በተባለችው ቻይና በ24 ሰዓት ውስጥ የተመዘገበው የ13 ሰዎች ሞት ነው። በቫይረሱ ደግሞ መጠቃታቸው የተነገረው 11 ሰዎች ብቻ ናቸው። - በአሜሪካ የብራዚል አምባሳደር በተደረገላቸው የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ቫይረሱ እንደሚገኝባቸው ተረጋግጧል። - በስፔን በ24 ሰዓት ውስጥ የ66 ሰዎች ሞት መመዝግቡን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥ 133 ደርሷል። - በአሜሪካ ዋሽንግተን ስቴት በ24 ሰዓት ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የስድስት ሰዎች ሞት ተመዝግቧል። - ፖላንድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ወደሀገሯ የሚገቡ የውጭ ሀገር ዜጎችን ለማገድ መወሰኗ ተሰምቷል። ፖላንድ ውስጥ በ24 ሰዓት አዲስ 16 የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ተመዝግቧል። - ዴንማርክ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለውጭ ሀገር ዜጎች ደንበሯን እንደዘጋች በይፋ አሳውቃለች። ዴንማርክ ውሥጥ 804 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል። - በፈረንሳይ የ18 ሰዎች ሞት መመዝገቡን ተከትሎ አጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 79 ደርሰዋል። በሀገሪቱ ከ3,661 ተጠቂዎች አሉ።